Saturday, November 23, 2024
spot_img

ሲኖዶሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ በመንበረ ፓትርያርኩ እንዲገኙ ጥሪ እንዲተላለፍላቸው መወሰኑ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥር 28 2014 ― የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ እንዲገኙ ጥሪ እንዲተላለፍላቸው መወሰኑ ተሰምቷል፡፡

በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር የሚወያው ሲኖዶሱ፣ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ በመንበረ ፓትሪያርኩ እንዲገኙ ያለው የካቲት 4፣ 2014 ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬተርያት ባለፈው ረቡእ ይፋ ባደረገው መረጃ፣ በእለቱ በከተማ አስተዳደሩ ኃላፊዎች እና በሲኖዶሱ መካከል ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በላከው መልእክት በስብሰባው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲያዝ በመጠየቅ›› ስብሰባው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ቅዱስ ሲኖዶሱ የከተማ አስተዳደሩ ስላወጣው መረጃ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም ነበር፡፡     

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img