Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሲኖዶሱ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለመወያየት ለዛሬ የያዙት ቀጠሮ ሳይሳካ መቅረቱን የከተማ አስተደዳሩ አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥር 25 2014 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለመወያየት በዛሬው እለት የያዙት ቀጠሮ ሳይሳካ መቅረቱን የከተማው አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬተርያት አሳውቋል፡፡

የፕሬስ ሴክሬተርያቱ ባሰፈረው መረጃ ለዛሬ በተያዘው ቀጠሮ መሠረት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ‹‹ቀጠሮ በተያዘበት ቦታና ሰአት የተገኙ ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶሱ በላከው መልእክት ዛሬ በስብሰባው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲያዝ በመጠየቅ›› የዛሬው ስብሰባ ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አያይዞም ‹‹እንደ ሁልጊዜውም ሁሉ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ለመወያየት እና አብሮ ለመስራት በማንኛውም ሁኔታና ሰአት ዝግጁ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን›› ብሏል፡፡

የቀጠሮውን መቅረት በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ ያለው ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img