Saturday, November 23, 2024
spot_img

አሜሪካ፤ አልሸባብ የኢትዮጵያና ሶማሊላንድ ስምምነት የፈጠረውን ውጥረት ለተዋጊዎች ምልመላ እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀበት ነው አለች

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ጥር 10፣ 2016 – አሜሪካ አልሸባብ የኢትዮጵያና ሶማሊላንድን ስምምነት ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለተዋጊዎች ምልመላ መልካም አጋጣሚ አድርጎ እየተጠቀመበት ነው ያለችው በፕሬዝዳንቷ ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ ማይክ ሐመር በኩል ነው፡፡

ሐመር ይህን የተናገሩት ትላንት ሐሙስ ጥር 9፣ 2016 በኡጋንዳ ኢንቴቤ በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች ስብሰባ ላይ ነው፡፡ ልዩ ልኡኩ በዚሁ ወቅት አገራቸው አሜሪካ አሸባሪ የምትለው አልሸባብ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን የባህር ወደብ የመግባቢያ ስምምነት ለአዳዲስ ተዋጊዎች ምልመላ እንደ መልካም እየተጠቀመበት እንደሚገኝ ጠቋሚ ምልክቶች መታየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሐመር በንግግራቸው የመግባቢያ ስምምነቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የግዛቴ አካል ናት በሚለው የሶማሊያ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት መካከል የተፈጠረው ውጥረት አሜሪካን ጨምሮ ሌሎችም ‹‹በአልሸባብ ላይ እያደረጉ ያለውን ትግል ሊያደናቅፍ ይችላል የሚል ስጋት አለን›› ሲሉ አክለዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ ማይክ ሐመር በኩል የተንጸባረቀው የአልሸባብ ጉዳይ በአሜሪካ ባለሥልጣን ሲስተጋባ በሳምንቱ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ የአገሪቱ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የስትራቴጂክ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ጆን ኪርቢ በተመሳሳይ ከሰሞኑ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረው ነበር፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ታኅሣሥ 22፣2016 በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት ኢትዮጵያ ነጻ አገር መሆኗን ላወጀችው ሶማሊላንድ ዕውቅናን በመስጠት ከሶማሊላንድ የባሕር በር ትወስዳለች፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት የተቃወመውችው ሶማሊያ የግዛት አንድነቴን የሚጋፋ ነው ስትል ቆይታለች፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img