Saturday, November 23, 2024
spot_img

የዶላር ነገር

በዛሬ ዐርብ የካቲት 24፣ 2015 መደበኛ የአሜሪካ ዶላር ምንዛሬ መሠረት አንዱ ዶላር በ54.83 እንደሚሸጥ እና በ53.75 እንደሚገዛ ከንግድ ባንኮች መካከል በድንገት የመረጥነው ባንክ የመረጃ ማዕከል ያመለክታል፡፡ ነገር ግን በሀገር ውስጥ ያለው ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች በተለይም የግሎቹ ምንዛሬን ለሚጠይቋቸው ደንበኞች የሚያስከፍሉት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለምንዛሬው ካስቀመጠው ዕለታዊ መሸጫ የዋጋ ተመን በላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ እንደ ዋዜማ ራድዮ ዘገባ ከሆነ ለአንድ የአሜሪካ ዶላር ከግል ባንኮች እየተጠየቀ ያለው ኮሚሽን ከ55 ብር እስከ 60 ብር የሚደርስ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የአንድን የአሜሪካ ዶላር የባንኮች መሸጫ ዋጋ ከኮሚሽኑ ጋር ተደምሮ ከ110 እስከ 115 ብር አድርሶታል። ራድዮው ችግሩ ይህ ብቻ አለመሆኑንም ይጠቅሳል፡፡ አንድ ነጋዴ በድምሩ የተቀመጠውን ዋጋ አውጥቶም ቢሆን ምንዛሬውን እንደፈለገው አያገኝም፡፡ ለዚህ ሥራ የድለላ ሥራ ይሠራሉ የተባሉት የባንክ ሠራተኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ሠራተኞች በባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተቀማጭ ያላቸው ግለሰቦች እና ምንዛሬውን የሚፈልጉ ደንበኞችን ያገናኛሉ፡፡

በዘገባው አስተያየት የሰጡ ባለሞያዎች ለውጭ ምንዛሪ እየተከፈለ የሚገኘው ኮሚሽን ብሔራዊ ባንክ እያወጣው ካለው ዋጋ መብለጡ በኢትዮጵያ ያለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስከፊ ደረጃ መድረሱን አመላካች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አስመጪዎች ሀገር ውስጥ በብር ክፍያ ፈጽመው ውጭ ሀገር ባሉ ሰዎች ለሚፈልጉት እቃ በውጭ ምንዛሪ ክፍያ ተፈጽሞላቸው እቃ ለማስገባትም (በተለምዶ ሐዋላ የሚባለው) ለአንድ የአሜሪካ ዶላር በተመሳሳይ 105 ብር ደርሷ ተብሏል፡፡ በዚህ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ሰበብ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቀጣይ የማያባራ የዋጋ ንረት ሊጋፈጥ እንደሚችል የበርካቶች ስጋት ሆኗል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ የውጭ ምንዛሬን አብቃቅቶ ለመጠቀም በሚል ለ38 አይነት ምርቶች በባንኮች የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቀድ ቢያዝም ለዜጎች የፈየደው ነገር እንደሌለ እንደሌለ ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img