Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር በነገው እለት ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው

አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ ነሐሴ 28 2014 የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ የሆኑት ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ መሆኑን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

ልዩ ልዑኩ የኢትዮጵያ ጉዟቸውን የሚጀምሩት ነገ እሑድ ነሐሴ 29፣ 2014 ነው፡፡ ከተሾሙ ወዲህ ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ እና የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚያቀኑት ሐመር፤ ያገረሸው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ቆሞ የሰላም ንግግር እንዲጀመር ያሳስባሉ ተብሏል፡፡

እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ፤ ማይክ ሐመር በዚህ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር እንዲሁም ከሲቪል ማኅበራት እና ሌሎች የፖለቲካ ተዋንያን ጋር ውይይት ያካሄዳሉ፡፡

ማይክ ሐመር ደረጉት ከሳምታት በፊት ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት፤ ከአውሮፓ ህብረት አቻቸው አኔት ዌበር፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ሃና ቴት እንዲሁም ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የካናዳ እና ጣሊያን አምባሳደሮች እንዲሁም የአሜሪካ ተወካዮች ጋር በመሆን ወደ ትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ አቅንተው ክልሉን ከሚመራው ሕወሓት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img