Saturday, April 20, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ያለ መከሰስ መብት እንዲነሳ ጥያቄ ቀረበ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ሐምሌ 8 2014 ያለ መከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተጠየቀው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ዶክተር ሙሉቀን ሐፍቱ ናቸው፡፡

የምክር ቤት አባሉ ያለ መከሰስ መብት እንዲነሳ የተጠየቀው ባለፈው ሳምንት ከወጣው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር በተገናኘ ነው፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው የከተማ አስተዳደሩ የሕግ ከለላው ይነሳልን ጥያቄውን ለፍትሕ ሚኒስቴር ያቀረበው ግለሰቡ ከቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን ስልጣንና ሃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ጋር በተገናኘ ተፈጽሟል ባለው መጭበርበር አሁን ያለ መከሰሰስ መብታቸው ይነሳልኝ ካላቸው ዶክተር ሙለቀን ሐፍቱ በተጨማሪ ሌሎች 10 ባለሞያዎችና ኃላፊዎችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ረቡዕ ሐምሌ 6 በሰጡት መግለጫ በተፈጸመው የማጭበርበር ተግባር ምክንያት የወጣው ዕጣ እንዲሰረዝ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

2 COMMENTS

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img