(አምባ ዲጂታል) ሰኞ የካቲት 7፣ 2014 ― የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚገኙ የገለጸው የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ነው፡፡
ትላንት የካቲት 6፣ 2014 አዲስ አበባ መግባታቸው የተነገረው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ፣ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከአፍሪካ ሕብረት እና ከተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች እና ከሰብዓዊ ድርጅት አስተባባሪዎች ጋር ይገናኛሉ ተብሏል፡፡
የልዩ መልዕክተኛው የአዲስ አበባ ጉዞ ይፋ የመጣው አስራ አምስት ወራት ላስቆጠረው የትግራይ ጦርነት መፍትሔ ለማበጀት በመንግሥት እና በህወሓት መካከል መቀጠሉ በተገለጸበት ወቅት ነው።
ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ የተገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ በሰጡት መግለጫ ለሰላም ተስፋ ያላቸውን ተስፋ ‹‹በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ›› ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡