Sunday, September 22, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ ያገሩ ዜጎች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 13፣ 2014 ― በአዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ የአገሩ ዜጎች ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

ኤምባሲው በትዊተር ባሰፈረው ማሳሰቢያ፣ ዝርዝር ሁኔታዎችን ያልገለጸ ቢሆንም፣ የቱርክ ዜጎች አሁን ያሉ በረራዎችን ተጠቅመው ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ መክሯል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት መባባሱን ተከትሎ ከቀናት በፊት የአሜሪካ መንግሥት እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ ሌሎችም አገራት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዜጎቻቸውን እንዲወጡ አሳስበው ነበር፡፡

ከአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ተጨማሪ ስዊድን፣ ጀርመን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ሩሲያ ለዜጎቻቸው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ነገር ግን መንግሥት ግን እነዚህ አገራት ያስለላለፉት ዜጎቻቸውን ውጡ የሚል ማሳሰቢያ የተጋነነ ነው ሲል አጣጥሎታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img