Sunday, October 6, 2024
spot_img

አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በሌሎች ሰባት ክልሎች የመራጮች ምዝገባ ለአንድ ሳምንት ተራዘመ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 29፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ዐርብ ግንቦት 6 የመራጮች ምዝገባ ይጠናቅባቸዋል በተባሉት በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ጨምሮ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላ፣ በሐረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልሎች ምዝገባው ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ቀጥሎ እስክ ግነቦት 6፣ 2013 ድረስ እንዲከናወን ወስኗል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች እንደተመዘገቡ ያስታወቀው ምርጫ ቦርድ፣ በተጠቀሱት ክልሎች እና የከተማ መስተዳደሮች የምዝገበውን ቀን ለማራዘሙ ምክንያቶችን አስቀምጧል፡፡

ቦርዱ ካስቀመጣቸው ምክንያቶች መካከል የመራጮች ምዝገባ በተራዘመበት ወቅት ተደራራቢ የበአላት ቀናት መኖራቸው እና በዚያም የተነሳ በህጉ መሰረት ብሔራዊ በአላት ዝግ በመሆናቸው የመራጮች ምዝገባ ሊከናወን አለመቻሉን እንዲሁም የመራጮች ምዝገባ በተራዘመበት ወቅት 1 ሺሕ 500 መራጮች የመዘገቡ ጣቢያዎቸን ለይቶ ንኡስ ጣቢያዎችን የማደራጀት ሂደት ጊዜ መውሰዱን በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የመራጮች መጨናነቅ ምርጫ ጣቢያ ላይ መፈጠሩን ጠቅሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img